tangledgroup/tangled-llama-a-128k-base-v0.1
Text Generation
•
Updated
•
190
text
stringlengths 0
2.31k
|
---|
ተለዋዋጭ የግድግዳ አንግል ሙቅ አንቀሳቅሷል ቲ-አሞሌ አጥቅሼ ... |
አንቀሳቅሷል ብረት ድርድር |
የዳንኤል እይታዎች Daniel Kibret's views: ‹‹ታች በሌ›› |
የዛሬ ሃያ ዓመት ከኮተቤ መምህራን ኮሌጅ እንደተመረቅኩ የመምህርነት ሥራዬን የጀመርኩት እነዋሪ በምትባል በሰሜን ሸዋ ውስጥ ከምትገኛና ከአዲስ አበባ 165 ኪሎ ሜትር በምትርቅ ከተማ ውስጥ በሚገኝ ትምህርት ቤት ነበር፡፡ እነዋሪ ከመርሐቤቴ እስከ ዜና ማርቆስ የሚኖረው ቆለኛና ደገኛው ጅሩዬ የሚገናኙባት የቀለጠች የገበያ ከተማ ናት፡፡ በተለይም በፍራፍሬ ምርቷ ትታወቃለች፡፡ ኤፍሬም እሸቴ የእነዋሪን ሙዝ ‹ከማጠሯ መጎጠሯ› እያለ ይቀልድባት ነበር፡፡ |
ከእነዋሪ እየተነሣሁ እስከ ዠማ ወንዝ ድረስ ለሠርግም፣ ለንግሥም ቆላውን እወርድ ነበር፡፡ ገበሬዎቹ ከቆላው ይመጡና እኔን በቅሎ ላይ አውጥተው በትከሻቸው ላይ ውጅግራ ጠበንዣቸውን ደልደል አድርገው ተሸክመው የጋቢያቸውን ግማሽ ጠቅልለው አናታቸው ላይ በማስቀመጥ፣ ከግራና ከቀኝ በቅሎዋን እየነዱ፣ ያንን እንደ ያሬድ መዝሙር በጆሮ የሚንቆረቆረውን ወጋቸውን እያወጉ፣ እንደ ዝንጀሮ ገደሉን በኩራት ይወርዱታል፡፡ ተረታቸው፣ ቀረርቷቸው፣ ፉከራቸው፣ ዘፈናቸው፣ የታሪክ ትረካቸው፣ ስለ ጀግኖቻቸው የሚገጥሙት ግጥም አሁንም በጆሮዬ እንደ መስክ ነፋስ ሲያልፍ ይሰማኛል፡፡ |
አንድ ቀን ታድያ አይዋ ሰጥ አርጌ የሚባሉ ቆፍጣና ገበሬ አብረውን ወደ ዠማ ሲጓዙ ታች በሌ ስለሚባል ሽፍታ አወጉኝ፡፡ ታች በሌ በተለይ በሞረቶች ዘንድ በጣም የታወቀ አስቂኝ ሽፍታ ነው፡፡ አንድ ሰው ያላሰበበትን፣ ያልተዘጋጀበትንና ያለ ዐቅሙ የሆነውን ነገር ጀመረ ሲባል ዠማዎች ‹‹ምን የእርሱ ነገርኮ የታች በሌ ሽፍትነት ነው›› ይሉታል፡፡ አንድ ሰው በስሜት ብቻ ተነሣስቶ እንዴው የጀብደኛነትን ሥራ ሲሠራ፣ አንድን ነገር አስቦ ከመሥራት ይልቅ ከሠራ በኋላ ሲያስብ ዠማዎች እንዲሁ ‹ታች በሌ› ይሉታል፡፡ ለምን? |
ታች በሌ የዠማ ሰው ነው፡፡ የኖረው ከዛሬ ሁለት መቶ ዓመት በፊት በሸዋው አስፋ ወሰን ዘመን ነው አሉ፡፡ በዚያ ዘመን ሞረትን ይገዙት የነበሩት ጥዱ የተባሉ ኃይለኛ በላባት ነበሩ፡፡ እንዲያውም ጥዱና አስፋ ወሰን እርስ በርሳቸው የሚፎካከሩም የሚፈታተኑም ኃይለኞች ስለነበሩ ግጥሞቻቸው ዘመን ተሻግረው ደርሰውናል፡፡ አስፋ ወሰን ሞረትን ማስገበር ስለፈለጉ |
ብለው ለአዝማሪ ነገሩ አሉ፡፡ ይህን የሰሙት ጥዱም |
ብለው መለሱላቸው ይባላል፡፡ |
ጥዱ ኃይለኛ አስገባሪ፣ አስጨንቆ ገዥ ነበሩና ብዙ ገበሬዎችን እንደ ሰም አቅልጠው፣ እንደ ብረት ቀጥቅጠው፣ እንደ ጫማ ረግጠው ይገዙ ነበር፡፡ ከተገዥዎቹ ገበሬዎች አንዱ የነበረው ታች በሌ መረረው፡፡ በልጅነቱ በሰሜን ሸዋ በረሃዎችና ጫካዎች ሸፍተው ገዥዎችን ስላስጨነቁ ሽፍቶች እየሰማ ነበርና ያደገው መሸፈት አማረው፡፡ አንድ ቀን ከብት ይጠብቁ ለነበሩ እረኞች መሸፈቱን ነግሮ የአጎቱን ቁመህ ጠብቀኝ መንትፎ ሸፈተ፡፡ ሸፍቶም ጫካ ገባ፡፡ አገሩም ‹ታች በሌ ሸፈተ› እያለ ከሚዳ እስከ እነዋሪ አወጋ፡፡ አንዳንዱ አደነቀ፤ ዘፈነለት፤ አንዳንዱ ተጠራጠረ፣ አንገቱን ነቀነቀበት፡፡ ‹በምን ልቡ ነው የሸፈተው›› ያሉም ነበሩ፡፡ ጥዱም እገለዋለሁ ብለዋል ተባለ፡፡ |
ታች በሌ ዠማ ወንዝ በረሃ ውስጥ ወርዶ አንድ ጫካ ውስጥ ተቀመጠ፡፡ መጀመሪያ ስሙ በድፍን ሸዋ ሲገንን፣ ስሙ በየሠርግ ቤቱና በየድግስ ቤቱ የዘፈን መቋጠሪያ ሲሆን እየታየው ልቡ በደስታ ሞቆ ነበር፡፡ ዋል አደር ሲል ግን ታች በሌን ጥያቄዎች ጭንቅላቱን እየሞሉ ያስጨንቁት ነበር፡፡ ለመሆኑ በቂ ስንቅ ይዘሃል? የሸፈትከውኮ በጀግናው ጥዱ ላይ ነው፤ ለመሆኑ በቂ ጥይት ታጥቀሃል? ለመሆኑ ቢመጡብህ የምትሸሽበት የማምለጫ ስርጥ መርጠሃል? አንተ መንደርህ እያለህ አንድ ቆቅ እንኳን አድነህ የማታውቅ እንዴት ጥዱን ለመዋጋት ጫካ ገባህ? ለመሆኑ ዛሬ የታጠቅከውን ቁመህ ጠብቀኝ ተኩሰህበት ታውቃለህ? ቢበላሽ ማን ይጠግንልሃል? ከዛሬ በፊት ለመሆኑ ጫካ ውለህ አድረህ ታውቃለህ? ከአውሬ ጋር ታግለህ ታውቃለህ? |
እነዚህ ጥያቄዎች ጭንቅላቱን ሲወጥሩት ታች በሌ መልስ አልነበረውም፡፡ የዠማን በረሃ ወደ መርሐ ቤቴ ሲያልፍበትና ወደ ጅሩ ሲወጣበት እንጂ ውስጡ ገብቶ ሥር ማንሥሩን አይቶት አያውቅም፡፡ እንዲያውም አሁን ሲያስበው ትንሽ ፍርሃት ሳይኖርበት አይቀርም፡፤ እንደ ሌሎቹ እንኳን ቅራት (ከብትን በረሃ ውስጥ ሌሊት መጠበቅ) ለብቻው አድሮ አያውቅም፡፡ ደግሞ አሁን ሸፍቷልና የሚያወያየው እንኳን የለም፡፡ እየዋለ እያደረ ሃሳብ ሲበዛበት ታች በሌ ይጨንቀው ነበር፡፡ ሽፍትነት ሲያስቡትና ሲሸፍቱት አንድ አልሆነለትም፡፡ እርሱ እዚህ በረሃ ውስጥ ምን እንደሚያደርግ ጨንቆታል፣ እዚያ መንደር ውስጥ ግን በስሙ ይዘፈን ይሆናል፡፡ የልቡን ማን አየለት፡፡ ለእርሱ ከሚዘፍኑለት ስንቅና ትጥቅ ቢያቀብሉት ነበር የሚሻለው፡፡ |
ታች በሌ ለአንድ ሳምንት በረሃው ውስጥ ተቀመጠ፡፡ ስንቅና እድሜ እያደር ይቀላል እንዲሉ የያዘው ነገር ሁሉ እያደር ያልቅበት፣ እርሱም ብቸኛነትን አልለመደውም ነበርና እያደር ሆድ ይብሰው ጀመር፡፡ አንዳንዴም ሲያስበው መሸፈት እንዳልነበረበት ራሱን ይሞግታል፡፡ አሁን እንዴት አድርጎ ወደፊት መጓዝ እንደሚችል ያስባል፤ ግን ምንም ሃሳብ ሊመጣለት አልቻለም፡፡ ወደ ኋላ እንዳይመለስ ሰው ምን ይለዋል? አንዳንዴ የተወለደበትን ቀን ትቶ የሸፈተበትን ቀን ይረግማል፤ አንዳንዴ ደግሞ እንኳን ሸፈትኩ ይላል፡፡ ቢጠብቅ ቢጠብቅ ጥዱም ሆኑ የጥዱ አንጋቾች ወደ አካባቢው ዝር ሊሉ አልቻሉም፤ ታድያ ሳይዋጋ ሽፍታ ተብሎ እስከ መቼ ሊቀመጥ ነው፡፡ እንዲህ ከሆነኮ ጥቂት ቆይቶ ይረሳል፡፡ |
ታች በሌ እየቆየ ነገር ዓለሙ መረረው፤ መሸፈቱንን እንጂ ለምንና ምን ሊያደርግ እንደሸፈተ ለኅሊናው ማስረዳት አልቻለም፤ ቀጥሎ ምን እንደሚያደርግና ከዚያስ መጨረሻው ምን እንደሆነ ሊያውቀው አልቻለም፡፡ እገሌ ሸፈተ ሲባል እንጂ ሽፍትነት ምን እንደሆነ፣ ሸፍቶ ምን እንደሚደረግ በልቡ ምንም ነገር አልያዘም፡፡ |
አንድ ቀን ታች በሌ ድንገት የሚኖርበት መንደር ያለች ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በቅዳሴ ሰዓት ከች አለ፡፡ አገርም ጉድ አለ፡፡ ካህናቱም ጨዋውም እያየው አፉን ይዞ ቀረ፡፡ ታምር ተሰምቶ የሰንበት ቂጣ ሊታደል ሲል ታች በሌ ድንጋይ ይዞ ሕዝቡ እግር ሥር ወደቀና ይቅርታ ጠየቀ፡፡ ሰይጣን አሳስቶኝ ነው ብሎ በዚያ መከረኛ ላይ አላክኮ ካህናቱ ድንጋዩን አነሡለት፡፡ |
አንድ ሰሞን የታች በሌ ነገር የሞረቴ ሁሉ አፍ ማሟሻ ሆነ፡፡ ከዚያ በኋላ ለሞረቴ መሸፈት ቀላል አልሆነም፤ ‹‹ደግሞ እንደ ታች በሌ ሲርብህ እንዳትመጣ›› የሚባለው ብዙ ነው፡፡ እንዲያውም አንድ ሰው ሸፈተ ሲባል አቅራሪዎቹ |
ልብ ካልሸፈተ እግር አይሸፍትም ….. ሃ! |
እያሉ ይመክሩት ነበር፡፡ ታች በሌ ሳያስቡ ለሚወስኑና ሳያስቡ ለሚያደርጉ ሁሉ የሚሰጥ ቅጽል ሆነ፡፡ |
ታች በሌያዊ አስተሳሰብ የሀገራችን ተቋማት አንዱ ችግር ነው፡፡ አንዳንድ ፓርቲዎች፣ ማኅበራት፣ ድርጅቶች፣ ኩባንያዎችና ስብስቦች ሳይታሰቡ ተመሥርተው ሃሳብ የጠፋባቸው ናቸው፡፡ ለሃሳብ ተቋም ከመመሥረት ይልቅ ለተቋማቱ ነው ሃሳብ እየተፈለገ ያለው፡፡ ቁጭት ሁሉ፣ ብስጭት ሁሉ፣ ስብስብ ሁሉ፣ ገንዘብ ሁሉ፣ አጋጣሚ ሁሉ ድርጅት፣ ፓርቲ፣ ተቋም፣ ማኅበር ለመመሥረት መዋል የለበትም፡፡ እነ ዕገሌ ስለ መሠረቱ፣ እነ እገሌ ስለተሰባሰቡ፣ የዕገሌ አካባቢ ሰዎች በስማቸው ፓርቲ ስለመሠረቱ፣ የዚህ ዓይነት ሞያ ሰዎች ማኅበር ስላቋቀቋሙ፣ የዚያ ሀገር ሰዎች ኮሙኒቲ ስለ ፈጠሩ፣ እንቶኔና እንቶኔ ኩባንያ ስላቋቋሙ እኛም ማቋቋም የለብን፡፡ |
መጀመሪያ ሃሳብ ይቅደም፡፡ ማሰብ ማለት ደግሞ ሃሳብን ብልጭ ማድረግ ማለት አይደለም፡፡ ይህማ ታች በሌን መሆን ነው፡፡ ብልጭ ያለውን፣ ቁጭት የፈጠረውን ሁሉ ሳያስቡበት ተጣድፎ ማድረግ፡፡ ማሰብ እንዲህ አይደለም፤ ግራ ቀኝ የታሰበበት፣ የተጠናና የተነበበበት፣ ከቀደምቶች ልምድ የተቀሰመበት፣ ከተሳካላቸውም ካልተሳካላቸውም ትምህርት የተወሰደበት፣ እንዴት እንደሚኬድ፣ ግቡ ምን እንደሆነ፣ የተሻለው መንገድ የትኛው እንደሆነ፣ የሚያስፈልጉ ነገሮች ምን እንደሆኑ፣ ከነ ማን ጋር መተባበር እንደሚገባ፣ ምን ሊያጋጥም እንደሚችል፤የፍልስፍና መስፈንጠሪያው ምን እንደሆነ አጥልቆና አልቆ መመርመር ነው- ማሰብ፡፡ |
አንዳንድ ሰው አስቤያለሁ ሲል ‹‹ይህ ነገር በአእምሮዬ መጥቶልኛል›› ማለቱ ነው፡፡ ይህኮ ሰው በመሆኑ ብቻ የሚያጋጥመው ነው፡፡ በአምስቱ የስሜት ሕዋሳቱ መረጃዎች ወደ አእምሮው ሲገቡ ልክ በቁልፍ እንደሚነሣ መኪና ቅንጭሌውን ሊያስነሡት ይችሉ ይሆናል፡፡ ይህ ግን መኪናው በቁልፉ ስለተነሣ ብቻ ሄደ እንደማይባለው ሁሉ ሰውዬውም አሰበ አያስብለውም፡፡ መጀመሪያ የመኪናው ባትሪ ቀጥሎ ሞተሩ መነሣት አለበት፡፡ ሞተሩ ደግሞ ሌሎችን ሁሉ አንቀሳቅሶ ሙሉ መኪናው መሥራት አለበት፡፡ ያን ጊዜ መኪናው ሄደ ይባላል፡፡ |
ሰውም ሃሳብ ብልጭ ስላለለት፣ የሆነ ቁጭት ስለተፈጠረበት፣ ከሆነ ሰው አንዳች ነገር ስላገኝ፣ በአጋጣሚ አንድ መረጃ ስለደረሰው፣ ቅናት ስላደረበት፣ ዕድል ስለተፈጠረለት፣ ዘመዶቹ ክፈት እንረዳሃለን ስላሉት ብቻ ተቋም፣ ድርጅት፣ ፓርቲ፣ ማኅበር መመሥረት የለበትም፡፡ አንዳንዶች የሆነ ነገር ለማድረግ አስበው ከመሰባሰብ ይልቅ ተሰባስበው ምን እንናድርግ? ብለው ያስባሉ፡፡ አንዳንድ ፓርቲዎች እንደ ታች በሌ ሳያስቡ የሸፈቱ ናቸው፡፡ የተለየ ሃሳብ፣ የተለየ ፍልስፍና፣ የተለየ አቋም፣ የተለየ መንገድ ሳይኖራቸው እንዴው በፓርቲዎቻችን ቁጥር ላይ አንድ ለመጨመር ያህል ብቻ የተመሠረቱ፡፡ ፓርቲው ከተመሠረተ በኋላ ነው ፕሮግራም፣ መመሪያ፣ ፍልስፍና፣ መንገድ፣ የሚያዘጋጁት፡፡ በሃሳብ ስለማይመሠረቱ ከተመሠረቱ በኋላ በሃሳብ ይለያያሉ፡፡ ሳስበው እንዲያውም ለሁሉም ችግሮቻችን መፍትሔ ስጡ ስንባል ኮሚቴ ማቋቋም የሚቀናን ለማሰብ ጊዜ ስለማንሰጥ ይመስለኛል፡፡ የስብሰባ፣ሞቅታ የፈጠራቸው ኮሚቴዎች ሃሳብ አጥተው ሲላጉ አባሎቻቸውን አንጠባጥበው መቼ እንደፈረሱ እንኳን ሳይታወቅላቸው ይፈርሳሉ፡፡ ታች በሌዎች በቁጭት ብቻ ተነሥተው የመሠረቷቸው የሞያ ማኅበራትም ከዓመታዊ ጉባኤ ያለፈ ሃሳብ ሊመጣላቸው ስላልቻለ፡፡ በአንድ ሊቀ መንበር ሃያ ዓመት እያዘገሙ እንዴት ናችሁ? ሲባሉ ‹አለን›› እያሉ ካሉት በታች ከሞቱት በላይ ሆነው ይኖራሉ፡፡ |
አንዳንዶችም አሉ፤ ምን እንደሚጽፉ ሳያስቡ መጽሐፍ ለመጻፍ የሚነሡ፡፡ ምን እንደሚገጥሙ ሳያስቡ ግጥም ለማሳተም የሚውተረተሩ፡፡ ምን እንደሚያቀርቡ ሳያስቡ ፊልም ለማዘጋጀት ገንዘብ የሚያሰባስቡ፡፡ የተለየ ሃሳብ ሳይኖራቸው የሬዲዮ የዐየር ሰዓት የሚገዙ፡፡ ምን እንደሚጠይቁ ሳያስቡ የቃለ መጠይቅ ማይካቸውን ተጠያቂው ላይ የሚተክሉ ቀልደኞች፡፡ ለነገሩ በሠፈር አንድ ሱቅ ሲከፈት የሠፈሩ ሰው ሁሉ አጥሩን እየቀደደ ሱቅ መሥራት የተለመደበት ሀገር ውስጥ ነው ያለነው፡፡ ያዋጣል ወይ? ከጎረቤቴ በምን እለያለሁ? እኔ ምን አዲስ ነገር አመጣለሁ? ብሎ ሳያስብ ነው ሱቁን ቦግ የሚያደርገው፡፡ ሱቁን ከሠራና ዕቃ ካስገባ በኋላ ነው ማሰብ የሚጀምረው፡፡ ይህ ነገር ወደ ተቋሞቻችንም ተጋብቷል፡፡ ምን ተቋሞቻችን ብቻ ትዳሮቻችንም እንዲህ እየሆኑኮ ነው፡፡ ማግባት የሚፈልግ እንጂ እንዴትና ለምን እንደሚያገባ፣ የጋብቻው ጠባይና አካሄድ ምን እንደሚመስል አስቀድሞ የሚያስብ ጥቂቱ ነው፡፡ የሆነ ቦታ ለመሄድ እያሰብኩ ነው፤ የሆነ ነገር ሳልከፍት አልቀርም፤ አንድ የሆነ መጽሐፍ ልጽፍ እያሰብኩ ነው፤ የሚላችሁ ሰው ሳያስብ አንዳች ነገር ሊያደርግ የተዘጋጀ መሆን አለበት፡፡ |
አስቦ መሥራት እንጂ ሠርቶ ማሰብ ኪሣራው ብዙ ነው፡፡ ገበያ መውጣታቸውን እንጂ ምን ሊገዙ እንደወጡ፣ ቤት መሥራትና መግዛት እንጂ ምን ዓይነት ቤት እንደሚገዙ ወይም እንደሚሠሩ፣ ውጭ ሀገር መሄድ እንጂ ለምንና እንዴት እንደሚሄዱ፣ የማያስቡ አሉ፡፡ በአንዳንድ ሀገሮች የነበረውን መንግሥት ስለመቀየር እንጂ በቅያሪው ስለሚመጣው መንግሥት ስላልታሰበበት የመጣው ከሄደው የባሰበት ጊዜ አለ፡፡ ለዚህ ነው ታች በሌያዊ የሆነውን መንገድ ትትን ሃሳብ ከተቋም ይቅደም የምለው፡፡ ሃሳብ ከድርጊት ይቅደም፡፡ ሃሳብ ከመመሪያም፣ ከዐዋጅም፣ ከማፍረስም፣ ከመሥራትም፣ ከመሸለምም፣ ከመቅጣትም፣ ከመሄድም ከመምጣትም ይቅደም ፡፡ |
አንድ ሰው እንዲያውም ይህንን ነግሮኛል፡፡ የአንድ ገበሬ ውሻ ሁልጊዜ መንገድ ዳር እየቆመ አላፊ አግዳሚውን መኪና ለመያዝ እየተከተለ ይጮኻል፡፡ የገበሬው ጓደኛ ይኼ የውሻው ጠባይ ይገርመዋል፡፡ አንድ ቀን ገበሬውን ‹‹ለመሆኑ ይኼ ውሻህ መኪናውን ተከትዬ እይዘዋለሁ ብሎ ነው እንዲህ መከራን የሚያየው?›› ይለዋል፡፡ ገበሬውም ሳቅ ብሎ ‹‹እኔ ለመያዝ መታገሉ አይደለም የሚያስገርመኝ፤ የሆነ ቀን ሊይዘው ይችላል፡፡ እኔን የሚገርመኝ መኪናውን ቢይዘው ምን እንደሚያደርገው ውሻው አለማሰቡ ነው›› አለው ይባላል፡፡ ታች በሌያዊ አስተሳሰብ ማለት ይህ አይደለም ታዲያ፡፡ |
Posted by ዳንኤል ክብረት |
በአንዳንድ ሀገሮች የነበረውን መንግሥት ስለመቀየር እንጂ በቅያሪው ስለሚመጣው መንግሥት ስላልታሰበበት የመጣው ከሄደው የባሰበት ጊዜ አለ፡፡ |
እሩቅ ሳትሔድ ግብፅን አታይም ! አታድርስ ነው። |
ሕልምና ትርጉም እንደ ፈቺው ይሎል እንዲህ ነው። |
አንድ ለራሴ! አመሰግናለሁ |
‹‹እኔ ለመያዝ መታገሉ አይደለም የሚያስገርመኝ፤ የሆነ ቀን ሊይዘው ይችላል፡፡ እኔን የሚገርመኝ መኪናውን ቢይዘው ምን እንደሚያደርገው ውሻው አለማሰቡ ነው›› |
ይህ ጉዳይ እኛ ዘንድም የሚከስትበት ጊዜ አለ:: ሁሉም ነገር በስሜት ያይደለ እየተስተዋለ ቢሆን መልካም ነው:: ዲያቆን ዳንኤል እናመስግናለን:: |
አንድ ቀን ገበሬውን ‹‹ለመሆኑ ይኼ ውሻህ መኪናውን ተከትዬ እይዘዋለሁ ብሎ ነው እንዲህ መከራን የሚያየው?›› ይለዋል፡፡ ገበሬውም ሳቅ ብሎ ‹‹እኔ ለመያዝ መታገሉ አይደለም የሚያስገርመኝ፤ የሆነ ቀን ሊይዘው ይችላል፡፡ እኔን የሚገርመኝ መኪናውን ቢይዘው ምን እንደሚያደርገው ውሻው አለማሰቡ ነው›› አለው ይባላል፡፡ ታች በሌያዊ አስተሳሰብ ማለት ይህ አይደለም ታዲያ፡፡ |
ታች በሌዎች በቁጭት ብቻ ተነሥተው የመሠረቷቸው የሞያ ማኅበራትም ከዓመታዊ ጉባኤ ያለፈ ሃሳብ ሊመጣላቸው ስላልቻለ፡፡ በአንድ ሊቀ መንበር ሃያ ዓመት እያዘገሙ እንዴት ናችሁ? ሲባሉ ‹አለን›› እያሉ ካሉት በታች ከሞቱት በላይ ሆነው ይኖራሉ፡፡ |
ኦ ዲ/ን ዳንኤል! ቃላቲከ ያጠልሉ አዕጽምተ ከመ ዜማ ያሬድ አቡከ፤ ወያስተፈሥሁ ልበ ከመ ወይን ዘቤተ እምከ፡፡እስተቲ |
እስቲ ለዲ/ን ዳንኤል አንዲት …የግእዝ ቅኔ |
ለተሳሳቱ ልቦች ይሁናቸዉ ስንቅ፡፡ |
ይህ እኔ የተረዳሁበት መንገድ ንዉ የቅኔ እዉቀት የለኝም ግን ለመርዳት እመክራለሁኝ፡፡ ከተሳሳትኩኝ ለመታረም ዝግጁ ነኝ፡፡ |
ስለታች በሌ ሳነብ አንድ ነገር አስታወስከኝ የአያቶቼን አገር ከዛሬ ሐያ አመት በፊት እንደዚህ አይነት ጨዋታዎችን ይነግሩኝ እና አውቅ ነበር የሚገርመው ነገር ከት/ቤት ጓደኞቼ ጋር በእድሜ እኩያ ከሆነው ማለት ነው የእኔ ነገር አይገጥም ነበር ሁል ጌዜ ነገርን በምሳሌ ስለሜናገሩ እኔም የእነሱ አባባል እንደልብስ ወርሼው ማለትን ነው አሁን እንደዚህ አይነት ነገር በምሳሌ የለምእኮ እንደው ደክመህ እንደነታች በሌ አባባል ለአሁን ትውልድ መሳቂያ ነው የሚሆኑት እኒስ የናፈቀኝ ከከተማው ሰው ይልቅ የገጠሩ ሕብረተሰብ ነው ሲያናግርሕ በፍቅር ሲጠላሕም በግልፅ ወደኋላ የሚባል ነገር የሌለበት ሕብረተሰብ የአሁን ትውልድ በሬ ካራጁ ይውላል ብቻ ነው እባክህ |
አስቦ መሥራት እንጂ ሠርቶ ማሰብ ኪሣራው ብዙ ነው፡፡ tikikil bilehal Dn. Daniel. enamesegnalen. |
ውጭ ሀገር መሄድ እንጂ ለምንና እንዴት እንደሚሄዱ፣ የማያስቡ አሉ ይህ መልዕክት በአብላጫው በውጭ ሃገር በስደት ላይ የምንገኘው ሁሉ ያካተተ ነው ማንም አስቦ አልሞ የተሰደደ አለ ለማለት ያቅታል ሁሉም ቢጠየቅ እኔ እኮ እንደዚህ አልመሰለኝም ነበር ስደት |
ሳስበው እንዲያውም ለሁሉም ችግሮቻችን መፍትሔ ስጡ ስንባል ኮሚቴ ማቋቋም የሚቀናን ለማሰብ ጊዜ ስለማንሰጥ ይመስለኛል፡፡ |
ወታደር ግርማ ወንድሙ ቄስ ሆነው ክርስቶስ የሰራቸውን ታኣምራት እሰራለሁ እያለ በህዝብ ሲጫወት: ይህ ሁሉ ግፍ ሲሰራ የቤተክርስቲያን አባቶች የት ሂደው ነበር:: |
ይህንን ቪዲዮ በድንብ አድርጋቹ ተመልከቱ፥፥ አስገራሚ ድራማ፥አንዱ ተዋናኝ በተለያዮ ጊዜ ትውናውን ሲሰራ ይመልከቱ:: |
“የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና።” 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ፥ምዕራፍ 1 ቁር 18 |
አስቦ መሥራት እንጂ ሠርቶ ማሰብ ኪሣራው ብዙ ነው |
ወንድም ዳንኤል በጣም ጥሩ ምክር ነው የመከርከን ግን ለሚገነዘብ እንጂ ለሌላው ወሬ ነው፡፡ ይሁንና እግዚአብሔር ወደፊትም ከአንተ ጋር ሆኖ ይህንን መንገድህን እስከፍፃሜው ያቅናልህ፡፡ ሌላው ግን የዲ/ን ዳንኤል ድረ ገጽ ብዙ አንባቢ አለው በማለት የማይገናኝ ሀሳብ ለማንሳት የሞከራችሁ ወገኖች ቆም ብላችሁ አስቡ፡፡ ታች በሌ መጀመሪያ መሸፈቱ ሳይሆን ብዙ ሳይደክም አቅሙን አውቆ መመለሱና ይቅርታ መጠየቁ ትልቅ ትምህርት ቤት ከመግባት በላይ መሆኑን ያስረዳናል፡፡ ስለ መልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ ለማውራት የፈለግከው ወይ ጠንቋይ፣ ወይ አስጠንቋይ፣ ወይ ባለዛር ውላጅ በመሆንህ በአንተ ላይ ያደረ አጋንንት አይነጥላ አዙረህ እንዳታይ እንደ ጋሪ ፈረስ ሸብቦ እየነዳህ ስለሆነ የእግዚአብሔርን ኃይል በመርሳት ወታደር ነበር፣ነጋዴ፣ገበሬ እያልክ ብታወራ የምታመጣው የለም የዓለም ሕዝብ አንተ ከምትለው ሀሳብ ባለፈ በሲዲ ብቻ ሳይሆን በአካል ተገኝቶ በመረዳት ሕይወቱን ከሞተ ስጋ ብቻ ሳይሆን ከሞተ ነፍስም እያዳነ ነውና ንስሐ ገብተህ ሰይጣንን ክደህ በእግዚአብሔር መንገድ ብትሔድ ይሻላል እላለሁ፡፡ |
ግንኮ አንዳንዴ ማሰብ ማብዛትም የማያስፈልግበት ቦታ አለ፡፡ intuition, instinct ወይም gut reaction ይሉታል፡፡ብዙ ስታስብ ወይም ስታወራ ያደረከዉ ይመስልሃል፡፡ ከዚ ከዚ እንደ ታችበሌ ከስህተት መማር ሳይሻል አይቀርም፡፡ |
ወንድም ዳንኤል በጣም ጥሩ ምክር ነው |
ወንድም ዳንኤል በጣም ጥሩ ምክር ነው የመከርከን |
የተለየ ሃሳብ፣ የተለየ ፍልስፍና፣ የተለየ አቋም፣ የተለየ መንገድ ሳይኖራቸው እንዴው በፓርቲዎቻችን ቁጥር ላይ አንድ ለመጨመር ያህል ብቻ የተመሠረቱ፡፡ ፓርቲው ከተመሠረተ በኋላ ነው ፕሮግራም፣ መመሪያ፣ ፍልስፍና፣ መንገድ፣ የሚያዘጋጁት፡፡ በሃሳብ ስለማይመሠረቱ ከተመሠረቱ በኋላ በሃሳብ ይለያያሉ፡ |
click here for pdf የአንድ ትልቅ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበረ ሰው ከደርጅቱ ሲለቅ ለተተኪው ሰው ሦስት ደብዳቤዎችን በሦስት ፖስታዎች አሽጎ በላያቸውም ላይ 1፣ 2 ና 3 ቁጥር ጽፎ ሰጠው፡፡ ተ... |
- አዲስ የወጎች መጽሐፍ በቅርብ ቀን |
የ2007 ዓም የበጎ ሰው ሽልማት ፎቶዎች |
አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ |
ራእየ ዮሐንስ ክልስ ዕትም፤ ከልዩ ልዩ መረጃዎች እንደገና ተጠናቅሮ፣ ተብራርቶና ተዘጋጅቶ የቀረበ መጽሐፍ፤ |
ዋጋ 60 ብር ብቻ |
የበጎ ሰው ሽልማት ፳፻፮ ዓም |
‹አራቱ ኃያላን› በጎንደር |
እጨጌ ዕንባቆም የመናዊ- በመርካቶ ተክለ ሃይማኖት ተዘጋጅቶ የነበረው ልዩ መርሐ ግብር |
‹የዳንኤል ዕይታዎች› ሦስተኛ ዓመት አከባበር (ፎቶ) |
አንድ ሰርግ ውስጥ አንድ ሽማግሌ ሙሽሮቹን ሊመርቁ ቆሙና « አጣልቶ የሚያፋቅር፣ አጋጭቶ የሚያጣብቅ ፍቅር ይስጣችሁ » ብለው ሲመርቁ ሰማሁ፡፡ እስካሁን ብዙ ሠርግ ተገኝቼ ምርቃት ሰምቻለ... |
click here for pdf ክፍል አንድ በዚህ ዘመን በተደጋጋሚ ከሚነሡ መንፈሳውያን ጥቄዎች መካከል አንዱ የጥምቀትና አጥማቂዎች ጉዳይ ነው፡፡ ጥምቀት(የክርስትና ጥምቀትን አይመለከትም) በብሉይና በሐዲስ ኪዳ... |
click here for pdf ‹የክርስቶስ አንዲት በግ መከራን ስትቀበል ከማይ እኔ የበጉ እረኛ መከራ መቀበልን እመርጣለሁ› ይህንን የተናገረው ዮሐንስ አፈወርቅ ነበር፡፡ የቁስጥንጥንያዋ ንግሥት አውዶቅስያ... |
click here for pdf ትውፊታውያን የሀገራችን ሰዓሊዎች የማያመዛዝንን ሰው ሲስሉ አንድ ዓይና አድርገው ይስሉት ነበር፡፡ ሰፋ አድርጎ የማያይ፤ እውነትን በከፊል ብቻ የሚቀበላት፤ ከሚያውቀው ውጭ ሌላ ነገር ... |
click here for pdf እየሰማሁት ያለሁትን ነገር ለማመን ረዥም ሰዓት ፈጅቶብኛል፡፡ ቆይቼ ደግሞ ምናለ ውሸት በሆነ እላለሁ፡፡ አቶ መለስ ዜናዊን በዚህ ሁኔታ ማጣት አልነበረብንም፡፡ እንደ ሰው የተሳሳቷቸውን... |
ሁሉ በሽተኛ ሁሉ ራሴን ባይ በቤታችን ደኅና መጥፋቱ ነወይ የሚል የበገና ዘለሰኛ አለ፡፡ አሁን ያለችውን ሀገራችንን ቀድሞ ያየ ደራሲ መሆን አለበት የገጠመው፡፡ በሀገሪቱ ውስጥ ጤነኛ አካል የጠፋ ይመስላል፡፡ ... |
click here (ክፍል ሁለት) 1. ተአምራት ማድረግ የምን ውጤት ነው? ተአምራት ማድረግ ከሁለት ነገሮች ሊመጣ ይችላል፡፡ ከመንፈሳዊ ብቃትና ከሰይጣን አሠራር፡፡ በክርስትና ሕይወቱ የበረታ ሰ... |
አንድ መዝገብ ለዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ታሪክ |
የደጃዝማች ገርማሜ የሕይወት ታሪክ ተጻፈ ከቀኛዝማች ኃይሌ ዘለቃ 1937 ዓ.ም 1. ባለ ታሪኩ ይህ ቀጥሎ የቀረበው በእጅ የተጻፈ ታሪካዊ መዝገብ የዐፄ ምኒልክን መንግሥት በሸዋዎች ብርታት(በ... |
የ፳፻፱ ዓ.ም. የበጎ ሰው ሽልማት እጩዎች |
መንግሥታዊ የሥራ ኃላፊነትን በብቃት መወጣት ዘርፍ 1. ዶ/ር መስፍን አርአያ (ለብዙ ዓመታት የዐማኑኤል ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ሆነው ያገ... |
ጉዞ - ወደ ምድር ጥግ( ክፍል አንድ) |
ወላጆች፡- ሁለት ጉዳዮች አሉኝ |
ለሁለተኛ ጊዜ ታተመ |
ስለ ቅዱስ መስቀል የዛሬ 600 ዓመት የተጻፈ መጽሐፍ |
ኢትዮጵያ - ቦይንግ |
ቦይንግ 747-8፣ ለመገጣጠም ብቻ 4 ወር የፈጀ አውሮፕላን ነው፡፡ ስድስት ሚሊዮን የሚገጣጠሙ ክፍሎች አሉት፡፡ በተለያየ የዓለም ክፍሎች ሆነው ከጥቃቅን እስከ ግዙፍ፣ ከመካኒካል እስከ ኤሌክትሪካል የሚያመርቱ ከ... |
አንድ ነን ብዙዎች፤ አንዶችም ብዙ ነን |
የተፈጥሮ ሳይንስ ሊቃውንት ‹ዓለም በብዙ መልኩ የምትገለጥ ዉሑድ ዓለም ናት› ይላሉ፡፡ የተለያዩ የዓለም ከዊኖች ልዩ ልዩ ይምሰሉ እንጂ የአንዱ ዓለም ክፍሎች ናቸው፡፡ ከአንዱ ዓለም ጋር ተዋሕደውም የሚኖሩ ናቸው፡፡ ... |
እንደ ኖኅ ወይም እንደ ዮናስ |
ከሚያብዱት ጋር ከማበድ ይልቅ ከአጥሩ ዘለቅ ብለው አይተው ትውልድን የሚያስጠነቅቁ ሰዎች፣ ሁለት ዓይነት ዕጣ ፈንታ አላቸው፡፡ ወይ እንደ ኖኅ አልያም እንደ ዮናስ፡፡ ኖኅ በምድር ላይ ሊመጣ ያለውን የጥፋት ውኃ ዐ... |
አንድ ቅቤ አምራች ገበሬና ዳቦ አምራች ነጋዴ እንደ አጋጣሚ ድግስ ላይ ተገናኝተው ያወራሉ፡፡ በጨዋታቸው በጣም ስለተግባቡ ከዚህ በኋላ አጋጣሚ ፈጥረው ለመገናኘት ይስማማሉ፡፡ ነጋዴው ጠዋት ጠዋት 300 ግራም ዳቦ ... |
ታዋቂው የሥነ ልቡና ምሁር ሮልፍ ዶብሊ ‹አጥርቶ የማሰብ ጥበብ› በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ እንዲህ ይላሉ፡፡ እንበልና አንተ የመድኃኒት አስተዳደር ኃላፊ ነህ፡፡ ለረዥም ግዜ ታምሞ የአልጋ ቁራኛ ለሆነ ሰው የሚሰጥ... |
መስተጋብር፡- አማራጭ አይደለም ሕልውና ነው |
እጅግ ተቀራራቢ የሆነ ዘረመል ያላቸው(የቅርብ አያት ካላቸው) ወገኖች በሚመሠርቱት ግንኙነት ዝርያ የሚፈጠርበት ሂደት ኢንብሪዲንግ( Inbreeding ) ይባላል፡፡ በዚህ መልኩ የሚፈጠሩ ዝርያዎች ተፈጥ ሯዊ ጥንካሬያ... |
ሸዋ፡- የጥንትና ዛሬ መገናኛ |
ዛሬ በተለምዶ ‹ሸዋ› እየተባለ የሚጠራውና ወደ ስድስት በሚጠጉ ዞኖች የተከፋፈለው የመሐል ኢትዮጵያ ክፍልን ታሪክ መረዳት የኢትዮጵያን ሕዝብ የውሕደት ታሪክ ለመረዳት ዓይነተኛ ማሳያ ነው፡፡ በሰሜን በዓባይ ወንዝና በ... |
የዳንኤል እይታዎች Daniel Kibret's views: ሐል ፋር የመጠለያ ጣቢያ |
በሱዳን በረሃ ተጉዘው የሰሐራን በረሐ እንደ ግመል ያቋርጣሉ፡፡ ረሃቡ፣ ጥማቱ በትግል እና በወኔ ይታለፋል፡፡ በየመንገዱ መኪና ሲበላሽ መቆሙ፣ ከፖሊሶች ለመደበቅ በየተራራው ሥር ከአንድ ቀን እስከ ለሁለት ሳምንት ያለ ምግብ መቀመጡ፤ በየቀኑ ብር ጨምሩ ከሚሉ አሻጋሪዎች ጋር መጨቃጨቁ ይታለፍና ሊቢያ ይገባል፡፡ |
ከሊቢያ ፖሊሶች ተደብቆ፤ በማይታወቅ ቤት ውስጥ ከርሞ፣ በሌሊት ጀልባ ላይ ወጥቶ በሜዲትራንያን ባሕር ላይ ጉዞ ይጀመራል፡፡ በሕይወት እና በሞት መካከል እየተጓዙ፣ ከተሰበረ ኮምፓስ ጋር እየታገሉ፤ ልምድ በሌለው ካፒቴን እየተመሩ፤ በእግዚአብሔር ቸርነት ከባሕር አውሬ ተርፎ ማልታ ይገባል፡፡ |
ማልታ ላይ ደግሞ በፖሊስ ተይዞ መጀመርያ ሐል ፋር እሥር ቤት detention center ከዓመት እና ከሁለት ዓመት በኋላ ሲወጡ ደግሞ ወደ ሐል ፋር መጠለያ የድንኳን ካምፕ ይገባል፡፡ እሥር ቤቱ ዙርያው በግንብ እና በሽቦ የታጠረ ሲሆን አንዳንዶች እየዘለሉ፣ ሌሎች ዘመናቸውን ጨርሰው ወጥተው በአሁኑ ጊዜ ምንም አበሻ በውስጡ የለበትም፡፡ |
የመጠለያ ጣቢያው ውስጡ በኮንቴይነር እና በአረጁ ድንኳኖች የተሞላ ነው፡፡ ኮንቴይነሮቹ በቅርብ እንደ መጡ ሰምቻለሁ፡፡ ድንኳኖቹ ግን ራሳቸው እርጅናቸውን ይመሰክራሉ፡፡ በተለይም በዚህ ያረጀ ድንኳን ውስጥ አጥንት ድረስ በሚገባውና «ያገሬ ብርድ ማረኝ» በሚያሰኘው የማልታ የክረምቱ ብርድ እንዴት ሆኖ ሊኖርበት እንደሚችል መድኃኔዓለም ይወቅ፡፡ |
በአሁኑ ጊዜ እዚህ መጠለያ የሚኖር አበሻ የለም፡፡ ሁሉም ጥለውት ወጥተው በየሥራቸው ተሠማርተዋል፡፡ እኔ ግን የታሪካችን አካል ነውና በቪዲዮ እና ፎቶ አስቀርቼዋለሁ፡፡ |
እንዲህ ተሰቃይተው እና መከራ ተቀብለው እዚህ ማልታ የደረሱት ሁሉ በአንድ ነገር ያስገርሙኛል፡፡ ሁሉም ለወላጆቻቸው እና ለእኅት ወንድሞቻቸው ያስባሉ፡፡ እነርሱ ያዩትን መከራ ሳያዩ እዚያው በሀገራቸው ሊረዷቸው ደፋ ቀና ይላሉ፡፡ እንዲህ በመከራ ደርሰው ለቤተሰቦቻቸው ገንዘብ ይልካሉ፡፡ ከዚህ በላይ ምን ደግነት አለ? የሚልኩት ገንዘብ እኮ የላብ ሳይሆን የደም ዋጋ ነው፡፡ |
Posted by ዳንኤል ክብረት |
ውድ ዳንኤል በጣም ኣሳጠርከው::ይህ የባህር ኃየሎቹ ዜና መሆኑ ነው፤ በቀላሉ ሲታወስና "ማሽላ ሆዷ እያረረ" በሚባለው የብሶት ትረካችንና አነጋገራችን ሲወሳ ማለት ነው:: እንጂ የእነርሱ ብሶት እና መከራስ ተነግሮ አያልቅም:: ከዚህ ሁሉ አልፈው ደግሞ ለኃይማኖት ያላቸው ቅንነትና ታዛዥነት እንዳንተ ቦታው ላይ ቆሞ ላስተዋለ ሰው እውነት ለመናገር በራሱ ከባድ የተግባር ትምህርት ነው:: ልክ ገጠራማው ኢትዮጵያ ውስጥ እንደምታየው ሰው ሁሉ ዝቅ ብለው ሲታዘዙልህ፤ ለሃገሩ ባዕድነት እንዳይሰማህ የሚያደርጉልህ መስተንግዶና የሚያሳዩህ ወንድማዊ ፍቅር ሁለም በልብ ላይ ተጽፎ የሚቀር ነው:: ስለዚህ እነዚህ ወገኖቻችን ቢጻፍላቸው ቢተረክላቸው ያንሳል:: የህን ያህልም ለእኛና መሰሎቻችን በማስተዋወቅህ መድኃኔዓለም ይስጥህ እያልኩ እስቲ ከእነርሱ ኋላ ሊቢያ ስለቀሩት አንዳንድ መረጃ ማግኘት ከተቻለ ጠይቃቸው፤ ምክንያቱም ዛሬ ሊቢያ " ቀን ደርሶ አምባ ሊፈርስ" ነውና:: |
ይህን ጽሑፍ የሚያነብ ሰው “ማዕበሉ ወደ መርከቢቷ እንዲገባ ያደረገው ማን ነው?” ከሚለው ይልቅ “ማዕበሉ ከዚህ በኋላ እንዳይገባ፣ የገባውም እንዲወጣ እኔ ምን ማድረግ አለብኝ?” ብሎ ቢያስብ መልካም ይመስለኛል፡፡ እርግጥ ነው “ማዕበሉ የትኛውን የመርከቧን አካል ገንጥሎ ገባ? ያ የመርከቧ አካል ክፍተት እንዲፈጥር ያደረገው ምንድን ነበር?” ብሎ መጠየቅና መመርመር ችግሩ ዳግም በሌሎች የመርከቧ ክፍሎች ላይ እንዳይፈጠር ለመጠንቀቅና የጎደለውን እየሞሉ፣ የጠመመውን እያቀኑ ለመሔድ እጅግ ወሳኝ ነው፡፡ ነገር ግን ጥፋተኛውን የመፈለግና የመቅጣት ሥራ መከወን ያለበት መጀመሪያ እየሰመጠች ያለችውን መርከብ ያለ ችግር መንሳፈፍ መቻሏን ማረጋገጥ ከተቻለ በኋላ ብቻ ነው፡፡ አጥፊውን ከመርከቧ ለማስወገድ መጀመሪያ የመርከቧ ህላዌ ወሳኝ ነው፡፡ በቅድሚያ ሁሉም የመርከቧ ተሳፋሪዎች በመደማመጥና በመተባበር ሊሠሩት የሚገባው ቀመር “መርከቢቱን እንዴት እናድናት?” የሚለውን ጥያቄ የሚመልስ እንጂ “አጥፊውን እንዴት እንቅጣው?” ላይ ያተኮረ መሆን የለበትም፡፡ መርከቧን ካዳንንና ሕይወታችንን ካተረፍን በኋላ አጥፊውን ብንፈልግ የመርከቧ ተራዳ (mast) ላይ እንሰቅለዋለን፡፡ መርከቧ ከሰጠመች ግን እንኳን ለቅጣት የሚሆን ተራዳ ነፍስ ለማትረፊያ የሚሆን መቆሚያ ስፍራም አናገኝም፡፡ ችግር ፈጣሪውም፣ ተቆጭዎቹም ወደ ባሕሩ እንወረወራለን፡፡ የሻርክ ቀለብስ ከመሆን ማን ያድነናል? |
The cc100-samples is a subset which contains first 10,000 lines of cc100.
To load a language which isn't part of the config, all you need to do is specify the language code in the config.
You can find the valid languages in Homepage section of Dataset Description: https://data.statmt.org/cc-100/
E.g.
dataset = load_dataset("cc100-samples", lang="en")
VALID_CODES = [
"am", "ar", "as", "az", "be", "bg", "bn", "bn_rom", "br", "bs", "ca", "cs", "cy", "da", "de",
"el", "en", "eo", "es", "et", "eu", "fa", "ff", "fi", "fr", "fy", "ga", "gd", "gl", "gn", "gu",
"ha", "he", "hi", "hi_rom", "hr", "ht", "hu", "hy", "id", "ig", "is", "it", "ja", "jv", "ka",
"kk", "km", "kn", "ko", "ku", "ky", "la", "lg", "li", "ln", "lo", "lt", "lv", "mg", "mk", "ml",
"mn", "mr", "ms", "my", "my_zaw", "ne", "nl", "no", "ns", "om", "or", "pa", "pl", "ps", "pt",
"qu", "rm", "ro", "ru", "sa", "si", "sc", "sd", "sk", "sl", "so", "sq", "sr", "ss", "su", "sv",
"sw", "ta", "ta_rom", "te", "te_rom", "th", "tl", "tn", "tr", "ug", "uk", "ur", "ur_rom", "uz",
"vi", "wo", "xh", "yi", "yo", "zh-Hans", "zh-Hant", "zu",
]
An example from the am
configuration:
{'id': '0', 'text': 'ተለዋዋጭ የግድግዳ አንግል ሙቅ አንቀሳቅሷል ቲ-አሞሌ አጥቅሼ ...\n'}
Each data point is a paragraph of text. The paragraphs are presented in the original (unshuffled) order. Documents are separated by a data point consisting of a single newline character.
The data fields are: